ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄና መልስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Friday, 18 May 2012
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

  • ይመዝገቡ

ስው በምድር ላይ እንዲኖር እግዚአብሄር የፈቀደለት የዕድሜ ዘመን ስንት ነው

ሰው በምድር ላይ እንዲኖር እግዚአብሄር የፈቀደለት የዕድሜ ዘመን ስንት ነው
1 ዓመት በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

+1 ድምጽ
ሰው በምድር ላይ እንዲኖር የተፈቀደለት እስከ 120 ዓመት ብቻ ነው፤
1 ዓመት በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
ብዙ እድሜያቸው ከ120 በላይ ያለፈ ሰዎችን ምድራችን አስተናግዳለች። ይህ ንግግርህ በሳይንስ፣ በታሪክና በመፅሓፍ ቅዱስም ጭምር ያልተደገፈ ነው። መጽሓፍ ቅዱስ እንዲህ የሚልበትን ስፍራ ብትጠቁም እንኳ ጥሩ ነበር። ይታረም!!!
ኦሪት ዘፍጥረት 6፡3፤ እግዚአብሔርም። መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና፤ ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት ይሆናሉ አለ።
«ሰው» ስትል የአዳምና የሔዋን ዘር ማለትህ ይመስለኛል። ከእናቱ ማህጸን ከወጣ ህጻን ጀምሮ በእርጅና ብዙ ዘመን በምድር ላይ እስካለ ሽማግሌ ድረስ ያለው ሁሉ የሰው ልጅ ነው። እናም ለእነዚህ የሰው ልጆች በምድር ላይ እንዲኖሩ የተፈቀደበት እድሜ ስንት ነው? ብትል መልሱ እድሜያቸው ከተወለዱበት አንስቶ እስከሚሞቱበት ቀን ድረስ ያለው ነው። በወርም፣በዓመትም፣ በዓመታትም ውስጥ እንዲኖር የተፈቀደለትን ኖሮ ይሞታል። ለሁሉም የሞት እድሜ በገደብ የተቀመጠ ስላይደለ እዚህ ድረስ ሁሉም ይቆያል፣ ከዚህም አያልፍም ሊባል አይችልም። ጥያቄህን ለመረዳት ስሞክር ምናልባት «የሰው ልጅ በዚህ ምድር ላይ ረጅም ዘመን ለመኖር የተፈቀደለት ቢሆን እስከስንት ዓመት ነው?» ማለት ፈልገህ ከሆነ ይህንኑ ግልጽ አድርግ!! ረጅሙን እድሜ ማቱሳላ 969 ዓመት መኖሩን አንብበናል። (ዘፍ 5፣27) ከዚያም ለጥፋት ውሃ ምክንያት በሆነው የሰው ኃጢአት ምክንያት 120 መድረሱን ብናነብም ይስሐቅ 180 ዓመት መኖር ችሏል። ከዚያም ወርዶ 70 ከበዛም 80 ዓመት ሲሆን ይህንን ካለፈ ይድሜው ትርፉ ድካምና መከራ እንደሆነ ነግሮናል። «የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንገሠጻለንና» መዝ 90፣10
ከዚህ ቃል የምንረዳው ከሰባ እስከ ሰማንያ ያለው ለሰው ትልቁና በቂው የእድሜ ዘመን ሆኖ ከሰማንያ ዓመት በኋላም መኖር የሚቻል ቢሆንም አኗኗሩ ግን ድካምና መከራ ያለበት መሆኑን ያሳየናል። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ቦታ ላይ «እድሜህ እንዲረዝም «እናትህንና አባትህን አክብር (ዘጸ 20፣12)፣ እድሜአችሁ እንዲረዝም እግዚአብሔር ባዘዛችሁ መንገድ ሂዱ(ዘዳ 5፣33)፣ እድሜአችሁ እንዲረዝም ትእዛዛቴን ሁሉ ጠብቁ(ዘዳ 11፣8-9)፣ በመንገዴ የሄድክ እንደሆነ እድሜህን አረዝመዋለሁ(1 ነገ 3፣14)፣ በእድሜህም ላይ 15 ዓመት እጨምራለሁ(2 ነገ 20፣6)
ልጄ ሆይ፥ ሕጌን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።ብዙ ዘመናትና ረጅም ዕድሜ ሰላምም ይጨምሩልሃልና(ምሳ 3፣1-2)
ስለሆነም እድሜ እግዚአብሔርን ከመፍራትና ትእዛዛቱን ከመጠበቅ የተነሳ ሊጨመር ይችላል። ስለዚህ የማንም ሰው እድሜ የሚታወቀውና የሚጨመረው በእግዚአብሔር ሕግ ሥር ነው። «የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥ የወሩም ቍጥር በአንተ ዘንድ ነው፥ እርሱም ሊተላለፈው የማይችለውን ዳርቻ አደረግህለት» ኢዮብ 14፣5

የተዛመዱ ጥያቄዎች

1 መልስ
5 ወራቶች በፊት መንፈሳዊ Bereket Tekle (120 ነጥቦች) የተጠየቀ
2 መልሶች
4 መልሶች
የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2012 by iyesus.com
Terms of use | Contact us