ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄና መልስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Friday, 18 May 2012
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

  • ይመዝገቡ

"ደካማው አትክልት ይበላል" ማለት ምን ማለት ነው?

ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል ሮሜ 14'2
2 ወራቶች በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

+1 ድምጽ
ደካማ የተባለው " ሁሉ ተፈቅዶ ሳለ ባለማመኑ ምክንያት አሁንም የቀድሞ የብሉይ ሥርዓት የሚያስፈራራውና ፍጹም እምነት የሌለውን ሰው በተመለከተ የተሰጠ ስያሜ ነው። ደካማው አትክልት የሚበላው እግዚአብሔርን ፈርቶ ሲሆን ሌላውም ከሕግ ነጻ እንደወጣ በማመኑ ምክንያት ያለፍርሃት የሚበላው እግዚአብሔርን እያመሰገነ ነው።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 14
1 በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ
2 ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል።
3 የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና

በቁጥር 1 ላይ እንደሚታየው የደከመ የተባለው በእምነት ስለደከመ ነው። ስለዚህ ደካማው እምነት የጎደለው ማለት ነው።

አመሰግናለሁ
ፋንታጎንስ
2 ወራቶች በፊት ቤሪያ (1,140 ነጥቦች) የተመለሰ
ወንድም ፋንታጎንስ

ለምን እንደዚ ይባላል ፤ ባንተ አባባል እኮ "አትክልት የሚበላው እምነት የጎደለው ነው" ትንሽ እንኮን ግር አይልሕም። ክመስለሕ "እኔ እንደተረዳሁት" እንኮን አትልም ነው ክምትል? ማንስ ሆነህ አንተ ይሕን አትክልት የሚበላ ስው "እምነት ጎደል" ትለዋለሕ?

ቃሉን ቀጥለን እናንበብ።

4 አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።

6 ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል፤ የሚበላም እግዚአብሔርን ያመሰግናልና ለጌታ ብሎ ይበላል፤ የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም እግዚአብሔርንም ያመሰግናል


እና እግዚአብሔርን ሊያመስግን አትክልት ቢበላ "እምነት ጎደል" ትለዋለሕን?

ሄኖክ
የወንድሜን መልስ የተረዳኽው ስላልመሰለኝ ጥቂት አስተያየት ልስጥበት
    1)መጀመሪያ መልሱን አስተውለህ ደግመህ ብታነበው ደስ ይለኛል
    2)
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 14፥
1 በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።2ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል። 3 የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።

እዚህ ላይ ላሰምርበት የምፈልገው... ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ .. የሚለውን ነው ይህ በአዲስ ኪዳን ወንጌል ያመነ ሰው ባህሪይ የሚገልጽ ነው ምክንያቱም ”… ሁሉ ተፈቅዶአል ግን ሁሉም አይጠቅምም…” የሚለው አቁዋም ላይ ነውና ይህ ሰው አትክልትም ይሁን ሌላ ነገር ቢበላ ነቀፈታ ወይም ሃጢያት የለበትም ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው። ከዚህ በመቀጠልም ” ደካማው ግን አትክልት ይበላል።” ማለትም እምነቱ ጠንካራ ያልሆነው ግን አትክልት ይበላል። ይህም ሰው ከቀድሞው የ አይሁድ ህግ ሙሉ በሙሉ ነጻ ያልወጣ ወይም እምነቱ የደከመ በመሆኑ ምክንያት በቀድሞው ልማድ ውስጥ እንዳለ ያሳያል ምክንያቱም ”… ሁሉ ተፈቅዶአል ግን ሁሉም አይጠቅምም…” በሚለው አካሄድ ሳይሆን አልተፈቀደም በሚለው መመሪያ ይመራልና። ያም ሆነ ይህ "የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።"
ስለሚል ሁለቱንም ማለትም በእምነቱ የበረታውንም ይሁን የደከመውን እግዚአብሔር የተቀበላቸው መሆኑን ያሳያል። ሁላችንም እኩል የሆነ የእምነት ጥንካሬ የለንምና አንዱ የደከመ አንዱ የበረታ የመሆኑ እውነታ አያስቆጣም።
ወደ ሮሜ ሰዎች 14፥1
በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።2ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል። 3 የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።
ፋንታጎስ ሳይሆን ቃሉ ነው የሚለው።
ፋንታጎንስ፣ ትክክል ብለሃል። ሁሉም ቢፈቀድ ሁሉም እንደማይጠቅም የማያውቅ ያገኘውን ይበላል። የሚበላው ከደካማ እምነቱ የተነሳ ነው። ስለዚህ አንተ የምታምን በእንደዚህ ዓይነቱ የእምነት ደካማ ሰው ላይ አትፍረድ! ይልሃል ወንጌል። ሌላው ደግሞ በወንጌል ቢያምንም ሁሉ በእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው የሚለውን ለመቀበል በፊት የነበረበትን የሕግ ትዕዛዝ ፈጽሞ ለመተው ስለሚቸገር ጥያቄና የስህተትን ሃሳብ የማያስነሳበትን አትክልት ብቻ ለመብላት ይገደዳል። ይህም በእምነቱ ደካማ ሰው ነው። አንደኛው እምነት የጎደለው ሲሆን ሌላኛው እምነት ቢኖረውም በእምነቱ የበሰለ አይደለም ማለት ይመስለኛል።

የተዛመዱ ጥያቄዎች

1 መልስ
1 ወር በፊት መንፈሳዊ ሳምራ (160 ነጥቦች) የተጠየቀ
1 መልስ
2 ወራቶች በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
2 መልሶች
2 ወራቶች በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2012 by iyesus.com
Terms of use | Contact us