ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄና መልስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Friday, 18 May 2012
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

  • ይመዝገቡ

ሉቃ22:35_38ጌታ አየሱስ ለምን ሰይፍ ግዙ አለ

ጌታ እየሱስ ለምን ሰይፍ ግዙ አላቸው? ከአመጸኞች ጋር የተቁጠረው በተሰቀለ ግዜ ነው ማር15:27_28
3 ወራቶች በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

+3 ድምጾች
ኢየሱስ ሐዋርያትን አስቀድሞ የላከው ወደአይሁዳውያን ነበር። ያንጊዜ ሐዋርያት ምንም ትርፍ ነገር እንዳይዙ አዟቸዋል። «እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፣ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ» ማቴ 10፣6
በስራችሁም ምግባችሁ ከምትሄዱበት ይሁን ሲል «ወርቅ ወይም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፣ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና» ማቴ 10፣9-10 በግልጽ ነግሯል።
ይሁን እንጂ የጠፉት የእስራኤል ቤት በአብዛኛው ቃሉን አልቀበል ካሉ በኋላ ሐዋርያትን ዳግመኛ የእስራኤል ወገን ወዳልሆኑት አሕዛብ ልኳቸዋል። «የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም፣ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው» ዮሐ 1፣11-12
ሐዋርያት ወደሁለተኛው ተልእኮ ሲሄዱ አህዛብ የሚጠብቁት መሲህ አልነበራቸውምና የሚያሰተምሩትም ትምህርት ለእስራኤል ቤት የተለየ ነው። የሚያመልኩት በልዩ ልዩ ጣዖትና የመናፍስት አሰራር፣ ለማይታወቅ አምላክ ወዘተ ዓይነት ልምምድ ውስጥ ስለነበሩ የሐዋርያት ተልእኰ ከባድ መሆኑ አይጠረጠርም። ረጅም ጉዞ ይጠብቃቸዋል፣ ከሀገራቸው ወጥተው ወደማያውቁት ህዝብ ሊሄዱ ነው። መከሩ ብዙ ስለሆነ ጌታም በሁለተኛው ተልእኰአቸው ወቅት «ደግሞም፦ ያለ ኮረጆና ያለ ከረጢት ያለ ጫማም በላክኋችሁ ጊዜ፥ አንዳች ጐደለባችሁን? አላቸው። እነርሱም፦ አንዳች እንኳ አሉ፣ እርሱም፦ አሁን ግን ኮረጆ ያለው ከእርሱ ጋር ይውሰድ፥ ከረጢትም ያለው እንዲሁ፤ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ» ሉቃ 22፣35-36
ወደ እስራኤላውያን (ወደወገኖቻቸው) ቤት በሄዱ ጊዜ ምንም እንዳይዙ ተነግሮአቸው፣ ምንም አልጎደለባቸውም ነበር። በሁለተኛው ተልእኮ(ወደአሕዛብ) የሚደረገው ግን በጉድለት የተሞላ ስለሆነ ያላችሁን ይዛችሁ ሂዱ ሲል አዟል። ጳውሎስም ይህንን የጉድለት ችግር ሲገልጽ እንዲህ ብሎታል። «እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፥ እንጠማለን፥ እንራቆታለን፥ እንጐሰማለን፥ እንንከራተታለን» 1ኛ ቆሮ 4፣11
ወደእስራኤል ቤት ሲሄዱ ምንም ሳይጎድልባቸው ያገለግሉ የነበረው ቀርቶ የእስራኤል ቤት ወዳልሆነው በሄዱ ጊዜ የሚጠብቁት ምንም ነገር ባለመኖሩ፣
«ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት፥ ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም»2ኛ ተሰ 3፣8 ሲል ጳውሎስ በግልጽ ተናግሯል።
እንደዚሁ ሁሉ ክርስቶስ ከሐዋርያት ጋር በስጋው ወራት በነበረ ጊዜ እንደአባት እንደመሪና እንደጌታ ይንከባከባቸው ስለነበር የሚያሳሰባቸውን ነገር ሁሉ በእርሱ ላይ ይጥሉ ነበር። እርሱ ክርስቶስ በሥጋው ከአጠገባቸው በሚለያቸው በሁለተኛው ተልእኰ ላይ ግን ራሳቸውን ችለው በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ወደ ሥልጣንና ኃላፊነት የሚገቡ በመሆኑ ተልእኰአቸውን የተለየ ያደርገዋል።
«አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም። ወዴት ትሄዳለህ? ብሎ የሚጠይቀኝ የለም፣ነገር ግን ይህን ስለ ተናገርኋችሁ ኀዘን በልባችሁ ሞልቶአል» ዮሐ 16፣5-6
አዎ ሐዋርያት ዶሮ ጫጩቶቿን እንደምትንከባከብ፣ እየተንከባከበ ሲመራቸው የነበረው ክርስቶስ የሚለያቸው ሰዓት መድረሱን በነገራቸው ሰዓት ልባቸው በሀዘን ተሞልቷል።
ስለሆነም ወደማያውቁት ሕዝብ ሲላኩ፣ ተልእኮአቸው ረጅምና መከራ የተሞላበት በመሆኑ፣ በዚያ ላይ ክርስቶስ የሚለያቸው በመሆኑ ሐዋርያት ራሳቸውን የሚከላከሉበትና ተልእኮአቸውን የሚጠብቁበት ሰይፍ የግድ ያስፈልጋቸው ነበር። ጌታ ያለውን ሁሉ ሽጦ ይህንን ሰይፍ ይግዛ ባለው ጊዜ ጴጥሮስ በዚህ ሁለት ሰይፍ አለን ያለው ዓይነት ሰይፍ አልነበረም። «እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ እነሆ፥ በዚህ ሁለት ሰይፎች አሉ አሉት። እርሱም፦ ይበቃል አላቸው» ሉቃ 22፣38
በሰዓቱ ግን እውነተኛውን ሰይፍ ሐዋርያት ያላቸውን ሁሉ ሽጠው ገዝተዋል። ስለክርስቶስ ዓለሙን ሁሉ ትተው ለተልእኮ በመውጣት የታጠቁት ሰይፍ «እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ»ዮሐ 14፤17
ይህ ሰይፍ ጴጥሮስን ጆሮ ከመቁረጥ በላይ ኃይል ሰጥቶታል።
«ሳትሸጠው የአንተ አልነበረምን? ከሸጥኸውስ በኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን? ይህን ነገር ስለ ምን በልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም አለው፣ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ ሞተም፤ በሰሙትም ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ» የሐዋ 5፣4-5
ጴጥሮስ ጆሮ የሚቆርጥ ምድራዊ ሰይፍ አላስፈለገውም። ጳውሎስም ቃሉን ከማስተማር ጋር የዚህ ሰይፍ ኃይል ጠቃሚ እንደሆነ ሲናገር እናገኘዋለን። «የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ነው እንጂ በቃል አይደለምና፣ምን ትወዳላችሁ? በበትር ወይስ በፍቅርና በየውሃት መንፈስ ልምጣባችሁን?» 1ቆሮ 4፣20-21
ስለዚህ ጠያቂያችን ጌታ ኢየሱስ ሰይፍ ግዙ ያለው ለዚህ ነው።
በሁለተኛ ደረጃ «ከዐመጸኞች ጋር ተቆጠረ» ለሚለው ሃሳብ መነሻችን ኢሳ 53፣12 ነው
1/ትንቢቱ አስቀድሞ ተነገሯል።
2/ ጌታ ራሱ «ከዓመፀኞች ጋር ተቈጠረ ተብሎ የተጻፈው በእኔ ሊፈጸም ግድ ነው» ብሏል።
3/ ይህም ትንቢት «በዚያን ጊዜ ሁለት ወንበዶች አንዱ በቀኝ አንዱም በግራ ከእርሱ ጋር ተሰቀሉ» ማቴ 27፣38 እንደተናገረው ተፈጸመ።
3 ወራቶች በፊት ስም-አልባ የተመለሰ

የተዛመዱ ጥያቄዎች

2 መልሶች
6 ወራቶች በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
1 መልስ
8 ወራቶች በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
1 መልስ
9 ወራቶች በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2012 by iyesus.com
Terms of use | Contact us