ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን
ዋና ገጽ
»
ጥያቄና መልስ
 
Friday, 18 May 2012
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን
Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ
Q&A
የእገዛ ገጽ
Help
ጥያቄዎች
ያልተመለሱ
መለያዎች
ተሳታፊዎች
ጥያቄ ይጠይቁ
ይግቡ(Login)
ይመዝገቡ
ሁሉም ምድቦች
መንፈሳዊ
(392)
ስለ እኛ
(11)
ቴክኒክ ነክ
(21)
ሌሎች
(24)
ሴቶች የቤተክርስቲያን መጋቢ (PASTOR) እና ሽማግሌ(ELDERS)ሆና ማገልገል ትችላለች ወይ?
http:
//
carm
.
org
/
should-women-be-pastors-and-elders
መሆን እንደማይችሉ አንብቤአለሁ። የማየው ደግሞ የተለየ ነው። ችግሩ ከወንጌል ቃል ግልጽ አለመሆን ወይስ ከሰዎች እንደሚስማማቸው መተርጎም
?
3 ወራቶች
በፊት
በ
መንፈሳዊ
በ
ስም-አልባ
የተጠየቀ
3 መልሶች
+1
ድምጽ
መልሱ አትችልም ነው። የማትችለው ከወንድ ስላለነሰች ወይም ስለተፈረደባት አይደለም። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለሆነ እንጂ! እግዚአብሔር ከአዳም ሥጋ ከፍሎ ረዳት እንድትሆንለት ሔዋንን መፍጠሩ አካሉ ስለሆነች ሁለቱ አንድ ይሆናሉ በሚል ቃል ለማያያዝ ነው። አዳም የተፈጠረው በመጀመሪያ በእግዚአብሔር መልክና እስትንፋስ ነው።የሁለተኛው ሰው
(
የሄዋን
)
ሥጋ መነሻው
(
የአዳም
)
ሥጋ ስለሆነ እንደአንድ አካሉ ትቆጠራለች እንጂ በሱ ላይ ስልጣን እንዳለው ሰው በራስዋ ስልጣን የላትም ። የወደቀው የአዳም የተነሳው በክርስቶስ እንደሆነና የቤተክርስቲያንም ራስ በመሆኑ፤የሴት ራስም አዳም ነው እንጂ ሔዋን አይደለችም።«ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና»ኤፌ5፣23 ራስ ለሆነው ወንድ የሴት ራስ የለውም። ስለዚህም በቤተክርስቲያን ውስጥ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ዲያቆናት ስለመሾም በተነገረው
(
1ጢሞ3፣2
)
(
ቲቶ 1፣6
)
(
1ጢሞ3፣12
)
የወንዶችን መመዘኛ ሲያስቀምጥ የአንድ ሴት ባል የሆኑ ይሁን አለ እንጂ የአንድ ባል፣ ሴት የሆነች አላለም። ከሓዋርያት አንድም ሴት አለመኖሩ ሴቶች ያላመኑ እንደነበር ሳይሆን የሚያሳየው የቤተክርስቲያን ሹመት የወንዶች መሆኑን ማሳያ ነው። አንድም ቦታ ይህንን አስመልክቶ የወንዶችን እንጂ የሴቶችን ሹመት መንፈስ ቅዱስ ያልገለጠልን ተሰውሮ እንዲቀርና እኛ የተሰወረውን ነገር ተመራምረን እንድንፈልግ የቃላት ጫወታ በመምረጥ አይደለም። ይልቁንም «ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም።አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች»1ጢሞ2፣12
-
13 ላይ በግልጽ ነግሮናል። የወንድ ራስ ክርስቶስ ነው፣ የሴት ራስ ደእሞ ወንድ ነው ካለ ሌላ የማሻሻያ መንገድ የለም። እውነቱን ባንቀበልም እውነቱ እውነት ሆኖ ይቀራል።
1ኛ ቆሮ11፥3
ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ።
አንዳንዶች ጳውሎስ በጌታ መንፈስ የሚናገር እንዳልነበር በመቁጠር ስለሴቶች የተናገረውን ሁሉ በዚያን ዘመን ላሉ ብቻ እንጂ በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ለዘመናት የቤተክርስቲያን ጥያቄዎች መልስ ሊሆን እንደማይችል አድርገው በመተርጎም የራሳቸውን ዓላማ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አድርገው ሲጠቀሙበት ይታያል። ጳውሎስ ግን ስለሴቶች በተናገረበት 1ኛ ቆሮ ምእራፍ 11 ላይ « እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ» ብሎ መጀመሩ የክርስቲያን ክርስቶስን መምሰል ነገር ለቆሮንቶስ ሰዎች ብቻ በመነገር የሚያበቃ አለመሆኑን ያሳየናል እንጂ እኔን ምሰሉ ባለበት አስተምህሮ የዚህ ዘመን ሰዎች የቆሮንቶሳዊ መልእክት አይመለከተንም ማለት ትክክል አይደለም። እሱም እንዲህ በማለት ያጠናክረዋል።«ዳሩ ግን ማንም ሊከራከር ቢፈቅድ፥ እኛ ወይም የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለ ልማድ የለንም» ቁ16
የእግዚአብሔር ቃል እውነት በሰዎች የተለጠጠ ትርጉም አይለወጥም።
ለወንድ ፣ሴት አካሉ ስለሆነች አካሉንም የሚጠላ ሰው ስለሌለ ልክ እንደራሱ ሊወዳት የግድ ነው። አካላት ተገጣጥመው አንድ ሙሉ ሰው እንደሚሆኑ ሁሉ የአንድ አካል ክፍሎች የሆኑት ሴትና ወንድ ሙሉ የሆነችው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ይሆናሉ።
1ኛ ቆሮ12፥20
«ዳሩ ግን አሁን ብልቶች ብዙዎች ናቸው አካል ግን አንድ ነው»
3 ወራቶች
በፊት
በ
ስም-አልባ
የተመለሰ
ከመጻፍ እየተቀስክ የምታወራቸው ነገሮች በራሳቸው እውነት ቢሆኑም መሰረታዊ አተረጓጎምህ ትክክል አይደለም እሺ አንተ እንደምትለው ከሆነ አንድ ጠንከር ያለ ነገር ላውራህ፡ እኛ ሁላችን በአዲስ ኪዳን ላይ አዲስ ፍጥረት ነን ስለ አዲስ ፍጥረት መጻፍ ሲናገር ''.......፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።....''ገላ 3.28
ወዳጄ እኛ ሁላችንም በክርስቶስ መንፈሳዊ ሰዎች ከሆንን መንፈስ ፆታ የለውም ሰው ነው ፆታ ያለው...በ እኛ የሚሰራው መንፈስ ቅዱስ ከሆነ እርሱ አይምሮ ውስጥ ፆታ የሚባል ነገር የለም እንደወደደ በ እኛ ይሰራል.....
1ኛ ቆሮ
11፥3
ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ።
እንዳንቺ/ተ አባባል ጳውሎስ የሴት ራስ ወንድ ነው ማለቱ ጭቆና ነው።
1 ኛ ቆሮ
11፥13
በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት ራስዋን ሳትሸፍን ወደ እግዚአብሔር ልትጸልይ ይገባታልን
?
ጳውሎስ
-
ሴት ጸጉሯን ተተኩሳ በጉባዔ እንዳትጸልይ መከልከሉ ስህተት ነው። ከከለከለ ወንዱንም መከልከል ነበረበት። ይህ ጭቆና ለቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ብቻ የተላለፈ በደል ነው። ወደ እኛ እንዳይደርስ በእኩልነት መብት ሽረነዋል ነው
?
የምትይው ወይስ የምትለው
?
በመንፈስ ቅዱስ የሚያስብ አእምሮ ውስጥ ጾታ የሚባል ነገር ወደ ግኡዝነት ተቀይሯል ነው
?
ወይስ ምንድነው
?
ሰው ስንል ሴትና ወንድ ነው። ይህንን እውነታ የሚክድ ሰው የት ሀገር እንዳለ አላውቅም።
አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች። ስለዚህ የሴት ራስ ወንድ ሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነታ ይህ ነው። ይህ እውነታ በሴቶች ማኅበር ውሳኔ ወይም በህገመንግስት ድንጋጌ አይሻርም። በክርስቶስ ሁሉም አንድ ሆነዋል ማለት የእግዚአብሔር ማስቀደምና ማስከተል ተፈጥሮ ተሽሮአል ማለት አይደለም።
አንድ ጥያቄ ላቅርብ፣ ከ12 ቱ ሐዋርያት አንድም የሴት ሐዋርያ አለመኖሩ
(
በወቅቱ ሴቶች በሀገሩ ስላልነበሩ ወይም ሴቶች ወንጌልን ለመቀበል የአእምሮ ዘገምተኞች ስለሆኑ ወይም በሴቶች ላይ የተደረገ አድልዎ በመሆኑ ወይም ወንዶቹ ሐዋርያት ሴቶቹን ሰለሚወክሉ ወይም ሁላችሁ በክርስቶስ አንድ ሰው ናቸው በማለት አሁን ያቀረባችሁትን ለመቀበል ባለመፈለግ ወይስ በሌላ ምክንያት
?
ከቶ በምን ምክንያት ይሆን ከ12 ቱ አንዱ እንኳን የሴት ሐዋርያ ያልነበረበትን ምክንያት መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ ማስረጃ እስኪ ንገረን!!!!!!
–1
ድምጽ
ወንዶች ቦታቸውን ለቀው መታዘዝ አቅቶአቸው እቢ ባሉ ግዜ ግን ለህዝቡ የሚራራ እግዚአብሄር ሴቶች አስነስቶ አይተናል በቃሉ። ዳብራ ከነብይነት ወደ ፈራጅ ነት
(
አለቅነት
)
እዲሁም በሎ የጦር መሪነት። ማርያም የምስራቹን ቃል ስታውጅ ለሃዋርያት ምን የሆን ያ የሚባለው
?
የምሰራቹን የወንጌል ተናጋሪ እም!! "በኢዮጴም ጣቢታ የሚሉአት
አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች
፥ ትርጓሜውም ዶርቃ ማለት ነው" ከ ወዶቹ እኩል በስምዋ የተጠራች ደቀመዝሙር ምንታደርግ ይሆን ነበር በዛ ዘመን በሀወትዋ ወይስ በሞትዋ የየሱስን አዳኝነት ውጣ ይሆን ዋይስ ተናግራያ ያ ሁሉ ህዝብ እፈልጋታለን ትነሳ ይሉት
??
ልድያም ልብዋን ከፍታ ለተቀበልችው እውነት በቤታን ከፍታ ወንደሞችን ሰብሰባ ምን የሆን ታደርግ የነበርው
????
ያንቃል ተናገር ይሆን ወይስ ውጣ ዝም
???
እነጴጥሮስ ሚስት ነበሪአቸው ነገር ገን የአቂላ ሚስት ጵርስቅላ ብቻናት ከባልዋ እኩል የተጠራች መሰደድዋ ከሮም ወደ ፍልፓይ ለተገለጠላት ቃል ተገዝታ የሆን ውይስ ዝምበላ
?
ለጢሞቲዋስ በአያትህ በሎይድ እና በእናትህም በኤውንቄ የተባለላቸው እነኝህ እናት እናልጆች ባሎቻቸው የትሄደው ነው
???
ለሱ እዲህ የባልው
"አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤
ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።
የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።" 2ጢሞ3፡14
-
16
ማቲዎስ 28፡19
-
20 "
እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።"
ጌታ ይህን ሲናገር የነብሩት ወንዶች ብቻ ነበሩን
????
"አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።"ገላ3፡28 ጳውሎስ የህን ማለቱን እረስቶስ ይሆን ለጢሞትዮስ ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም ያልው
?
በዚህም ዘመን ሆነ በዛኛው ይህን ቃል የማትታዘዝ ሴት አትኑር ነገር ግን ከክርስቶስ የተሰጣትን ትእዛስ ሰለ ስው ዝም የምትል ሴት በትኖር እርስዋ የእግዚአብሄር ፈርሃት እርቓታል እና ወዮላት።
"ጠርተውም በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩና
እንዳያስተምሩ
አዘዙአቸው።
ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው። እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እናንተን እንሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የሚገባ እንደ ሆነ ቍረጡ፤
እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም አሉአቸው።"
3 ወራቶች
በፊት
በ
ስም አልባ
(
7,060
ነጥቦች)
የተመለሰ
1/ «አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።"ገላ3፡28
ስላልከው ጉዳይ
----
ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በክርስቶስ ደም ነው። የሞተው ደግሞ ለዓለሙ ሁሉ እንጂ ለተወለደበት ለአይሁዳዊ ወገን አይደለም። ማንም ወደቤተክርስቲያን አንድነት የሚቀላቀለው ክርስቶስ ለኃጢአቱ እንደሞተለትና አዳኙ እንደሆነ በመቀበሉ እንጂ ግሪካዊ ወይም አይሁዳዊ ፣ ሴት ወይም ወንድ በመሆኑ አይደለም። በዚህ ልዩነት የለም። ቀድሞ የተመረጠው የእግዚአብሔር ህዝብ የሚባለው አይሁዳዊ ብቻ ነው።
«ባሪያዬ እስራኤል፥ የመረጥሁህ ያዕቆብ፥ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፥
አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና። አንተ ባሪያዬ ነህ፥ መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ»ኢሳ 41፣8
በክርስቶስ ሞት ያ የልዩነትና የኃጢአት ግድግዳ በእርቁ ውል ፈርሷል።
ወደ ሮሜ ሰዎች5፥10
«ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን» የእርቁ ውል ክርስቶስ ያባቱን ፈቃድ
(
ሞትን
)
ሊፈጽም አባቱ ደግሞ የልጁን ፈቃድ
(
ይቅር ሊለን
)
ሊፈጽም ነበር። አህዛብ ባለመገረዝ ሙታን የተባሉበት ዘመን አብቅቶ በአንድያ ልጁ ደም መፍሰስ እንዲያው የእግዚአብሔር ልጅነትን ሕይወት አገኙ።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች2፥13
«እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ» በዚህ ምንም ልዩነት የለም። አይሁዳዊ፣ግሪካዊ፣ ሴት ወንድ ብሎ ልዩነት የለም። ምክንያቱም አለ፣ ጳውሎስ ፣ «ሮሜ 3፥22
እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና»
ስለዚህ ወንድሜ የጠቀስከው ጥቅስ ስለአክሌስያ አንድነት እንጂ ስለቤተክርስቲያን ውስጥ ሹመት አይናገርምና ተሳስተህ፣ አታሳስት እልሃለሁ። ይህንን ጥቅስ ብዙዎች ለራሳቸው ሃሳብ ተርጉመው ሲጠቀሙበት ይታያል።
2/ ስለዶርቃ ደቀመዝሙርነት የጠቀስከውን በተመለከተ
-
ደቀመዝሙር ያልከው ትርጉም በግእዙ ተማሪ፣ የመምህሩ ተከታይ ማለት ነው። ግሪኩም ቢሆን «μαθητής» ማቴቴስ ይለዋል፣ ትርጉሙም ተማሪ፣ የመምህሩ ተከታይ ማለት ነው።
ሐዋርያ ማለት ደግሞ
(
ግእዙ
-
ሖረ፣ ሄደ፣ ይሐውር ይሄድ ዘንድ
)
ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን የተላከ፣ ሂያጅ፣ መልእክተኛ ማለት ነው። ግሪኩ ሐዋርያ የሚለውን ቃል ከሁለት ግስ ያጣመረው ሲሆን«στέλλω»ስቴሎ ማለት «መላክ» ሲሆን «από»አፖ ማለት ደግሞ «እንዲሄድ ማድረግ» ማለት ነው። ሲያያዝም «ἀπόστολος»አፖስቶሎስ ማለት መልእክተኛ፣ ተላኪ፣ መልእክት አድራሽ፣ የተላከ ሂያጅ ማለት ነው። ስለዚህ በደቀመዝሙርና በሐዋርያ መካከል ትልቅ ልዩነት እንዳለ መረዳት አለብን። ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከመላካቸውና በዓለሙ ሁሉ የመንግሥቱን ወንጌል ለማዳረስ ከኢየሩሳሌም ከመውጣታቸው በፊት የመምህሩ ተማሪዎች
(
ደቀመዛሙርት
)
ነበሩ። በኋላ ግን የተጣቸውን መልእክት ይዘው
(
ሐዋርያ
)
ሆነው እስከዓለም ዳርቻ ተላኩ።
ሉቃ11፥49
«ስለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች። ወደ እነርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፥ ከእነርሱም ይገድላሉ ያሳድዱማል»
ስለዚህ ዶርቃ ደቀመዝሙር ነበረች ማለት ሐዋርያ ነበረች ማለት ስላይደለ ይህንን ለመጥቀስ መነሻህ ትክክል አይደለም። ይልቁንም በሐዋርያት ትምህርት ስር ቃሉን የሰሙና የተቀበሉ ብዙ ደቀመዛሙርት ነበሩ። «
የሐ6፥7
«የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ» የሚለው ኃይለ ቃል የሚያሳየን ነገር ደቀመዛሙርትነት ቃሉን የሰሙና የተማሩ ለቃሉ የሚታዘዙ ሁሉ እንጂ «ዶርቃ» ብቻ አልነበረችም።
ከዚህ አንጻር ዶርቃ ደቀመዝሙር ሆነች ስትል ምን ሆነች ለማለት ፈልገህ በጽሁፍህ እንደገለጽካት አልገባኝም።
3/ ጵርስቅላን በተመለከተ የጠቀስከው
-
የአቂላን ሚስት የጵርስቅላን ታሪክ የምናገኘው ጳውሎስ በአቴና የአርዮስፋጎስ ብዙ አስተምሮ ከፈጸመ በኋላ አቴናን ለቆ ወደቆሮንቶስ ባቀናበት ወቅት ነው። አቂላ አይሁዳዊ ስለነበርና ቀላውዴዎስ ቄሳር ደግሞ አይሁዳዊ የሆነ ሁሉ ሮማን ለቆ እንዲወጣ ትእዛዝ ስለሰጠ አቂላ ሮማን ትቶ ወደግሪኳ ቆሮንቶስ መጥቶ ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር ድንኳን እየሰፋ ይኖር ነበር። ጳውሎስም ለይግባኙ ወደሮማ ሲያቀና ከእነጵርስቅላ ቤት በእንግድነት ተቀምጦ ድንኳን አብሮ እየሰፋ መቆየቱን እናነባለን። « ሥራቸውም አንድ ስለ ነበረ በእነርሱ ዘንድ ተቀምጦ በአንድ ላይ ሠሩ፤ ሥራቸው ድንኳን መስፋት ነበረና»የሐዋ 18፣3
ቤተክርስቲያንን እያሰፋና ወንጌልን እየሰበከ 6 ወራት ሲቆይ የጵርስቅላና የአቂላ የቅድስና ስራ የሚመሰከርለት እንደሆነ እንረዳለን። ጳውሎስ ወደሶሪያ ሲወርድ እንኳን አብረውት ወርደዋል። ከዚያም ሮም ደርሶ ያደረጉለትን አቀባበልና እስከሞት ድረስ ያደረጉለትን የቅድስና ስራ አስታውሶ በሮም መልእክቱ ሰላምታ አቅርቡልኝ ሲል እናገኘዋለን።
« በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤
እነርሱም ስለ ነፍሴ ነፍሳቸውን ለሞት አቀረቡ፥ የአሕዛብም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚያመሰግኑአቸው ናቸው እንጂ እኔ ብቻ አይደለሁም» ሮሜ16፣3
-
4
ይህን ማድረግ የክርስትና ግዴታ መሆኑን አምነው በመቀበል በቤተክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ መገኘት ለጵርስቅላም ሆነ ለአቂላ «የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፥ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል»ሉቃ 10፣16 ያለውን የወንጌል ቃል በተግባር ማሳየታቸውን ያስገነዝበናል።
ከዚያ በተረፈ ሐዋርያ ነበሩ ወይም በቤተክርስቲያን መጋቢነት ጳውሎስ ሾሟቸዋል የሚል ገጸ ንባብ የለም።
3/ማቴዎስ 28፡19
-
20 "እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ»
በመጥቀስ ያቀረብከው የጽሁፍ ዐውድ ለሴቶችም መብት ያግዘኛል ማለትህን እንመልከት
-
በመሰረቱ መመስከር፣ ቃሉን ማካፈል፣ወደድነት ሰዎችን ማምጣት የሁሉም አማኝ መንፈሳዊ ግዴታ መሆኑን ልንረዳ ይገባል። እያልን ያለነው ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ በመጋቢነት ወይም ሽማግሌ ሆኖ በማስተዳደር ወይም በኤጲስቆስነት ወይም በዲቁና ግን ከወንዶች በስተቀር ሴቶች መሆን አይችሉም ነው።
አንተ የጠቀስከውን የማቴዎስ ወንጌል ጥቅስ እንዳለ ብንቀበልህ አባባልህ የሚያሳየው ሁሉ አጥማቂ፤ ሁሉ ሐዋርያ መሆን ይችላል ወደሚል ድምዳሜ የሚያደርስ ነው። በዚህ የጥቅል አስተሳሰብ ድምዳሜህ ውስጥ ሴቶችን ለማካተት በመፈልግ መጥቀስህ ወደስህተት እንዳታመራ ስጋት አለኝ። ወንጌል ግን አንተ ሁሉን የጠቀለልክበትንና ሴቶችን የጨመርክበትን ጥቅስ ለይቶ ያስቀምጥልናል።
1ኛ ቆሮ12፥29
«ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን
?
ሁሉስ ነቢያት ናቸውን
?
ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን
?
ሁሉስ ተአምራትን ይሠራሉን
?
»
ሁሉ መሆን አይችሉም ካለ አንተ ሁሉን ለማካተት መሻትህ ዐውዱን ለልብህ መሻት ከማዋልህ በስተቀር «ሂዱና አስተምሩ» ሲል ሁሉም አስተማሪዎች ናቸው ማለቱ አይደለም።
4/ ማስረጃ፣
ሀ/ከሴት ወገን ሐዋርያ የተባለ ማንም የለም።አለ የሚል ካለ ማስረጃ ይቅረብ!
ለ/ ሽማግሌ
(
በመሰረቱ የወንድ አንቀጽ ነው
)
አሮጊት
(
ለሴት
)
በቤተክርስቲያን አስተዳደር ሽማግሌ መሆን የሚችሉት ወንዶች ብቻ ናቸው።
«በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው» የሐዋ14፣23
«ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ»የሐዋ15፣6
«በከተማዎችም ሲዞሩ በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የቈረጡትን ሥርዓት ይጠብቁ ዘንድ ሰጡአቸው»የሐዋ 16፣4
«በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን፥ በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል»1ጢሞ4፣14
«በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል»1ጢሞ5፣17
«ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ»ቲቶ1፣5
ሽማግሌዎች ልከኞች፥ ጭምቶች፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም ጤናሞች እንዲሆኑ ምከራቸው»ቲቶ2፣2
«እንግዲህ ስለ ትዳር ጉዳይ የፍርድ ቤት ቢያስፈልጋችሁ በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጆች አድርጋችሁ ታስቀምጣላችሁን
?
አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። እንደዚህ ነውን
?
በወንድሞች መካከል ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን
?
»1ቆሮ6፣4
ሐ/መጋቢ
(
ፓስተር
)
ማለት የግሪኩ ቃል«ποιμαινω» ፖይማይኖ ሲሆን ይህንንም ለሀዋርያው ጴጥሮስ ሲጠቀምበት እናገኛለን።
«ደግሞ ሁለተኛ። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን
?
አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው፣ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው»ዮሐ21፣16
-
17 በሚለው ቃል ውስጥ ለጴጥሮስ ጌታ ሲናገረው አሰማራ፣ ጠብቅ፣አሰማራ ሲል ሶስቴ ከሰጠው ቃል ውስጥ የክርስቶስን በጎች ከጠላት መጠበቅና በሚመገቡት መስክ ማሰማራት ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ይህ ማስማራት የሚለውን ቃል ግሪኩ «ፓይማይኖ» ሲለው፣
«ጌታም አለ። እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም መጋቢ ማን ነው
?
»ሉቃ 12፣42 የሚለውን ቃል ፍጻሜ ያሳየናል። ለዚህም አገልግሎት የሚመረጡትን ደግሞ በቀጣይነት ሲነግረን ህያው ቃሉ እንዲህ ሲል ያስረዳናል። «ኤጲስ ቆጶስ፥ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ፥ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ» ቲቶ1፣7
ስለሆነም ልባም መጋቢ ማን እንደሆነ ጌታ እራሱ ነግሮን ሲያበቃ፣ ልባም መጋቢ ራሱ ሾሞ አሳይቶናል። እንዲሁም የቤቱ መጋቢም ሲመረጥ ምን መምሰል እንዳለበትም አስቀምጦልናል። ከዚህ ውጪ የሌለ ነገር ለማምጣት ቃሉን መጨንቆር ትክክል አይደለም።
ሴት የወንድ አካል ነች፣ ማንም አካሉን እንደሚወድ ሁሉ ሚስቱን እንደራሱ ይወዳል። ሴት በቤተክርስቲያን ውስጥ ትልቅ ድርሻ አላት፣ሴት የሌለችበት ቤተክርስቲያን የለችንም። ወንድ አስቀድሞ በመፈጠሩ ብቻ የሴት ራስ ነው። የሴት ራስ መሆኑ የሴትን ታናሽነት አያሳይም። አዳም ከሴት ቀድሞ የእግዚአብሔር ልጅ ተባለ።«የእግዚአብሔር ልጅ»ሉቃ3፣38
ስለዚህም አካሉ ከሆነችው ከሴት አስቀድሞ በመገኘቱ የሴት ሁሉ ራስ ወንድ ሆነ። እንደዚሁ ክርስቶስ የሙታን ሁሉ በኩር በመሆኑ የቤተክርስቲያን ራስ ተባለ። «እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው» ቆላስ 1፣18
1 ቆሮ14፥34
ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ፤ ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና።
1 ጢሞ2
12 ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም።
13 አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች።
የሚለውን ቃል እንደሴቶች መጨቆኛ መሳሪያ አድርገው የሚመለከቱ የሃይማኖት ፖለቲከኞች በመጋቢነት፣ በሽማግሌነት፣ በሊቀጳጳስነት፣ በሐዋርያነት፤ በአጥማቂነት ሲልኩ ይታያሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ለራስ እንዲመች አድርጎ በመተርጎምና በመሸቃቀጥ የተነሳ ሰማያዊቱ አንዲት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድሪቱ ላይ በሺህ አይጥና ድመት በሆኑ አንጃዎች ተከፋፍላለች። ዛሬም የምናየው ያንን ነው።
theological
knowledge
ወደዛ ጣለውና
ከመጻፍ እየተቀስክ የምታወራቸው ነገሮች በራሳቸው እውነት ቢሆኑም መሰረታዊ አተረጓጎምህ ትክክል አይደለም እሺ አንተ እንደምትለው ከሆነ አንድ ጠንከር ያለ ነገር ላውራህ፡ እኛ ሁላችን በአዲስ ኪዳን ላይ አዲስ ፍጥረት ነን ስለ አዲስ ፍጥረት መጻፍ ሲናገር ''.......፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።....''ገላ 3.28
ወዳጄ እኛ ሁላችንም በክርስቶስ መንፈሳዊ ሰዎች ከሆንን መንፈስ ፆታ የለውም ሰው ነው ፆታ ያለው...በ እኛ የሚሰራው መንፈስ ቅዱስ ከሆነ እርሱ አይምሮ ውስጥ ፆታ የሚባል ነገር የለም እንደወደደ በ እኛ ይሰራል.....
አዳምን ከምድር አፈር፣ ሔዋንን ከአዳም ሥጋ የፈጠረ መንፈስ ቅዱስ አንድ ጊዜና ከተመሳሳይ ነገር አለመፍጠሩ ተሳስቷል
?
እያልሽ ያለሽው ይህንን እኔ አስተካክየዋለሁ ነው!!!
–1
ድምጽ
ሰላም ሰላማችሁ ይብዛ
በጣም ይቅርታ አድርግልኝ አንተን ወንድሜን ለዘላልም በምድርም በሰማይም ይማንለያውን የማሳዘንም ሆነ ይማናደድ ሃስቡም የለኝም ግን ቃሉን በዝግታ በናየው ጥሩ ነው።
በመጀምሪያ ማስረጃ የለም የሴት ደቀመዛሙር ላልከው፦
"በኢዮጴም ጣቢታ የሚሉአት አንዲት
ደቀ መዝሙር ነበረች
፥ ትርጓሜውም ዶርቃ ማለት ነው፤ እርስዋም መልካም ነገር የሞላባት ምጽዋትም የምታደርግ ነበረች" ሐዋ9፡36 ኦርጅናል ትርጉሙ የሴት ደቀመዛሙር ማለት ነው ከእስዋ በቀር ይህቃል ሌላቦታ አይገኝም
mathetria
math-ay
'
-tree-ah
would
you
please
kindly
look
in
to
this
word
find
the
meaning
the
word
above
it
was
found
on
strong
'
s
Hebrew
/
Greek
dictionary
.
ሁለተኛው ሽማግሌ ውንድ እንጂ ሴት አይደላም ላከው መቸም መጸሃፍ ቅዱስ መጀመሪያ በአማርኛ እዳልተጻፍ ሁላችንም እናውቃለን ስለዚህ በቀላሉ አዮታ ላይ ኦርጅናል ትርጉም መፈልግ አያዳግትም እና
diakonos
dee-ak
'
-on-os
በእንግሊዝኛው
deacon
or
deaconess
እኛሽማግሌዎች ብለን የምንጠራችው ወንድና ሴትን የሚያካትት ነው። 1ጢሞ3፡8 ይመልከቱ
"ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፥ ባልም ሚስቱን አይተዋት ብዬ የተጋቡትን አዛቸዋለሁ፥
እኔ ግን አላዝም፥ ጌታ እንጂ።
"1ቆሮ7፡10
-
11 ብሎ ሲል የሚቀጥለው ላይ ግን
1ጢሞ2፡ 12 "ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን
አልፈቅድም
።" ይህን ግን እራሱ ሲያዝ ነው የምናጘኘው ሁሉም የጳውሎስ ደብዳቤዎች ባይሆኑም በዙዎቹ ለትጠየቀው ጥያቄ መልስ የሰጠባቸው ናቸው ማለት ስለሁኔታዎች ደብዳቤ ተጽፎለት የመለሳቸው ማለት ነው። ሰለዝህ ለምን እደመለሰው ባናውቅም ይህ መልስ አስፈልጋል ሰለ ቃሉ እግዚአብሄርን እና መሰግናለን ነገር ግን ወንጌላችን ሴቶችን
exclusive
የሚያደርግ አይደላም። ይህን ካልኩ ይበቃል አምሰግናለሁ
May
God
bless
you
.
3 ወራቶች
በፊት
በ
ስም አልባ
(
7,060
ነጥቦች)
የተመለሰ
የሴት ደቀመዝሙር የለችም አላልኩም። የሴት ሐዋርያ የለችም ብያለሁ። ጽሁፌን በደንብ አላነበብክም ወይም ያነበብከውን አላስተዋልክም። የደቀ መዝሙርንና የሐዋርያነትን ልዩነት ለይቼ ስላስቀመጥኩልህ በደንብ አንብብ ምክሬ ነው። ደቀመዝሙርነት ለመማር ከመፈለግ የሚመጣ ማንነት ሲሆን ሐዋርያነት ከምርጫ የሚመጣ ተልእኮ ነው። ዝርዝሩን ከላይ ስላስቀመጥኩ እዚህ ላይ አልደግምም።
ዲያቆን ለሴትም ለወንድም ሹመት ያገለግላል ያልከው ትልቅ ስህተት ነው። ጳውሎስ አንቀጹን ለይቶ ለወንድ መሆኑን ሲናገር «የአንድ ሴት ባል ይሁን» ብሏል። ሴቷም ዲያቆን የአንድ ሴት ባል ትሁን ልትል ነው ወይስ ጳውሎስ ያልገለጠው ስውር ነገር ላንተ ተገልጦ የአንድ ባል ሚስት ናት ልትለን ነው
?
ዲያቆን የሚለውን ግሪኩ ለይቶ በወንድ አንቀጽ
(
διάκονος
)
ዲያቆኖስ ሲለው የዲያቆኑን ሚስት ራሷን ያለምንም ሹመት
(
διακόνισσα
)
ዲያቆኒሳ በማለት ይጠራታል። ዲያቆን ማለት አገልጋይ ማለት እንደመሆኑ መጠን ለሴት አንቀጽ «ዲያቆናዊት» የሚለው ቃል የዋለው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን እሱም በሮሜ 16፣1 ላይ ለፌቤን አገልግሎት በተገለጸው ቃል ነው። ይህንን ተከትለው ፌቤንን ዲያቆናዊት ስላለ ለዚህ ሹመት ሴቶችም ይገባቸዋል የሚሉ የነገረ መለኮት ምሁራን እንደመኖራቸው መጠን በሉቃስ ወንጌል 8፣3 ላይ «የሄሮድስ አዛዥ የኩዛ ሚስት ዮሐናም ሶስናም ብዙዎች ሌሎችም ሆነው በገንዘባቸው ያገለግሉት ነበር» በሚለው ሐረግ ውስጥ «ያገለግሉት» ነበር የሚለው ቃል ለፌቤን በተነገረው ዓይነት «ዲያቆንዮ» በማለት ማስቀመጡ በቤተክርስቲያን ውስጥ በዲቁና ሹመት ይሰሩ ነበር ማለት ባለመሆኑ የሴት ዲቁና የገቢርና ተገብሮ ጉዳይ እንጂ የሹመትን ጉዳይ አያመለክትም በማለት ይከራከራሉ። ሹመቱን
(
አድራጊውን
)
ሲሆን ለማን እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦ ድርጊቱን ወይም አገልግሎቱንና ተሳትፎውን በተመለከተም ቃሉ ጥቅም ላይ መዋሉን እናያለን። ቃሉ ጥቅም ላይ መዋሉ በራሱ ሹመትን ለሁሉም እንደሚዳረስ አያሳይም።
የሆኖ ሆኖ ጳውሎስ በግልጽ ያላስቀመጠው መንፈስ ቅዱስ ስላልገለጸለትና የመገለጹን ጉድለት እኛ ለመሙላት በመሞከር ቃላት መጫር ተገቢ አይደለም።
የሴት ደቀመዛሙርት የለም ለዚህ ማስረጃ አምጣ ብዬ አልጠየኩም ነው የምተለው
?
ከሆነ ጌታ የባርክህ እዝህ ጋ አቆማለሁ። ነገር ግን አዎ ብያለሁ ነገር ግን ማለት የፈልግሁት ሃውርያ ነው የምትል ከሆነ እቀጥላለሁ። ቃሉን አውቆ ለክርክ ቃሉን የሚቀር ሰው ጋር በዙ ማለት አልችለም ። ይቅርታ።
የመጀምሪያውን ያነበብክ አልመሰለግንም
"ወንዶች ቦታቸውን ለቀው መታዘዝ አቅቶአቸው እቢ ባሉ ግዜ ግን ለህዝቡ የሚራራ እግዚአብሄር ሴቶች አስነስቶ አይተናል በቃሉ።"
All
I
am
saying
is
God
can
do
any
thing
if
you
want
to
box
HIM
go
head
do
it
.
That
is
what
is
happening
in
USA
and
it
will
be
until
Men
get
up
lead
the
generation
to
righteousness
God
will
rise
up
women
and
children
.
Other
wise
we
are
losing
to
Muslims
to
gay
and
many
other
things
as
the
man
goes
so
is
his
household
and
the
household
make
up
the
village
and
.....
one
man
decision
to
walk
godly
will
will
change
the
nation
.
My
brother
let
us
arise
do
the
will
of
God
.
God
is
going
to
do
HIS
work
with
us
or
without
us
.
let
us
be
a
workers
on
HIS
field
. መከሩ በዙ ነው ሰራተኞ እድንሆን ይገባናል እና።
የተዛመዱ ጥያቄዎች
1
መልስ
በመንፈስ ቅዱስ ያልተጠመቀ ሰዉ የቤተክርስቲያን አገልጋይ መሆን ይችላል ወይ?
3 ወራቶች
በፊት
በ
መንፈሳዊ
በ
ስም-አልባ
የተጠየቀ
2
መልሶች
ሀኖክ በይሁዳ መጽሕፍ የተናገረው ትንቢት አለ. እና ትንቢተ ሀኖክ መጽሃፍ መኖር አለበት ወይ አብራሩልን
6 ወራቶች
በፊት
በ
መንፈሳዊ
በ
ስም-አልባ
የተጠየቀ
1
መልስ
ሳልጠመቅ ማገልገል እችላለሁ?
6 ወራቶች
በፊት
በ
መንፈሳዊ
በ
ስም-አልባ
የተጠየቀ
2
መልሶች
የሰናፍጭ ቅንጣት እንዴት የሰማይ ወፎችን ማስፈር ትችላለች?
1 ወር
በፊት
በ
መንፈሳዊ
በ
ደጀብርሃን
(
1,080
ነጥቦች)
የተጠየቀ
1
መልስ
ከመጽሃፍ ቅዱስ ዉጭ ያሉ የቤተክርስቲያን ታሪኮችን ምን ያህል ማመን ይገባናል?
5 ወራቶች
በፊት
በ
መንፈሳዊ
በ
ችሊ
(
220
ነጥቦች)
የተጠየቀ
የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም
ኢሜል አድራሻዎ
ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2012 by iyesus.com
Terms of use
|
Contact us