ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄና መልስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Friday, 18 May 2012
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

  • ይመዝገቡ

ሁለት አማልክት አልሆኑም ታዲያ?

ይህ አምድ ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ውይስ ፈራጅ .....? በሚለው መማማር በቀጣይነት ለጠየኩት መልስ በማጣቴ እንደአዲስ ልጠይቅ ሆንዋል። ስለዚህ የዛ ተክታይ አርገው ካዩት ቡሃላ መልስ ይስጡ።

እምላክ ይባርክልኝ!


ለኔ ጥያቄ መልስ የሚስጠኝ ነው ያጣሁት ክጥይቄው በፊት ግን አላማችን/ፍላጎታችን መማማር ይሁን።

እኔ እንደሚገባኝ አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ ስው ሆኖ ፍጽሙን የአምላክነት ባህሪዩን ክስብእና(ስው ክመሆን)ጋ ያዋሃደዉ እግዚአብሄር ኣብ ለኛ ካለው ጽኑ የአባትነት ፍቅር ነው። አዎ ታላቁ ሊቀ ካህናችን እንደግናም ፍጹሙ አምላካችን መድሃንያለም ክርስቶስ በብሉይ ዘመን ያጣነውን መለኮታዊ በረከት ያስመልስልን ዘንድ አምላክ ሰው ሁነ። (አዎ የ አምላክ ልጅ)አምላክ የሆነው እሱ ጌታችን መደሃኒታችን እና አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው።

ሁላችንም እንደምንስማማበት አንድ አምላክ በሃዲስም በብሉይም አብን ያምለክታል። በተመሳሳይ መልኩ ግን የክርስቶስ አምላክነትም የሚያጠያይቅ አደለም፡፡

ስለዚህ አብ አምላክ ነው ወልድም አምልክ ነው። ሁለት አማልክት አሉን ማለት ስለሆነብኝ ጉዳዩ እርስ በራሱ ይጣላብኛል። በሌላ አባባል " የኢየሱስ ቦታ ከአብ እኩል ሳይሆን በአንዱ አምላክ በአብና በሰው መካከል ነው። የአንዱ አምላክና የሰውም ባህርይ ስላለው በሁለቱ መካከል ሊቆም የሚችል እውነተኛ ሊቀካህን ነው።" የምንል "ሊቀ ካህን" ነዉ አልቀ። አምላክ አይደለም። ማለታችን አይደልምን? ምክነያቱም 1+1=2 ነው እንጂ 1+1= 2 እና 3 ሊሆን አይችልም።

የክርስቶስን አምላክንቱን ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ያለምንም ጥያቄ እናምናለን። ግሩም ጌታችንአምላክ ነው።
መ/ቅ አንድ አምላክ ስለመኖሩ ይጠቅሳል ያዛልም። (ክአስርቱ ተዛዛት አንዱ )ስልዚህ አብ አምላክ ነው መድሃንያለም ክረስቶስ አምላክ ነው። ሁለት አማልክት አልኖሩንም?? እንዴትስ እራሳችንን አንድ አምላከ ክሚለው እምነት ጋር እናስታረቃልን?

መድሃኒያለም ክርስቶስ አማልጅ ክሆነ አምላክንቱ ምኑ ላይ ነው?

በ እርግጥ ጢሞ2፤5 ን እንደሚጠቅሱ አይጠፋኝም ንገር ግን ጌታችን ክ እርግት(ከአረገ) ቡሃላ እንደሚማልድ መ/ቅ ካሳየ እርዳታዎን እፈልጋልሁ። ለፍርድ እንደሚመጣ ግን ሁላችንም አይጠፋንም። የዮሐንስ ወንጌል 5፡ 27 "የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው።28-29 በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ።
30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።"


በዚህ አጋጣሚ እውቀትን ፍለጋ እንጂ እንዱን ከዛ ጎራ እኔ ወዲህ ሆኜ የማይጠቅም ሙግት ፈልጌ ኣደለም። ለሙግት የሚብቃም እውቀት እንዳለኝ አላቅም። ለኔ ይህ ጉዳይ መደሃኒታችንን ና አምላካችን ተገቢ የክብር ቦታውን የሚመለከት ስልሆነ ልንጠነቀቅ ና ልናቅ ይግባል።

ለጠየኩዋቸው ጥያቄወች ቀጥተኛ መልስ የሚስጡኝን አመስግናልሁ፡፡ ሰለስላሴ ያነሳሁት ነገር የለምና ለግዜው እሱን ባናነሳ።
4 ወራቶች በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
ውድ ዮናዔል

"የጨበጥኩትን መንፈሳዊ ሰላሜን በጥርጣሬ መበረዝ ስለማልፍልግ የምትለውን ለመመርመር እና ለማጥናት ፈጽሞ ፍላጎትና ተነሳሽነት የለኝም አይኖረኝምም።"
በሚለው ንግግርዎ ቀጥተኛና የማያሻማ አቋምዎን ስለገለጹልኝ አመሰግናለሁ።
እኔም ማንም ሰላሙን እንዲያጣ ፍላጎት የለኝም!!! ሁላችሁን በማመልከው በጌታዬና በአምላኬ በኢየሱስ ፍቅር ይቅርታ እጠይቃለሁ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ!! አሜን!

ወዳችኋለሁ
በጌታ ወንድማችሁ!!
ውድ ቤሪያ

ስለ መልሶት እና ሃሳቤን ስለ መረዳቶት ምስጋናዬን እነሆኝ!! ይሁን እንጂ የነበሩትን መማማሮች እና (ጥያቄ ና መልሶች)ውስጥ ቀንሶ ማስቀረት እና የመረጡትን መተዉ ሌሎች ሰዎች ሊማሩበት ወይም መልስ/አስተያይት ሊሰጡበት እንዲችሉ አያድደርግም። ሌላው በፍጹም ይቅርታ የሚያስጠይቅ ነገር ስላልነበረ በወንድማዊ ፍቅር የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማዎት ካደርኩዎት ይቅርታ መጠየቁ የኔ ይሁን። በ አጭሩ እኔ ማለት የፈለኩት የ ጌታችንን እና የመደሃኒታችንን የ እየሱስ ክርስቶስን እንደ አብ ሁሉ ያለውን መለኮታዊ ክብር ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚያስገባ ጉዳይ ሲመጣ መንፈሳዊ ሰላሜን (የጌታችንን የ እየሱስ ክርስቶስን ማን መሆን)በጥርጣሬ ውስጥ መክተት እድል ልሰጠው የምፍልግው ጉዳይ አደለም ለማለት ብቻ ነው። መልሶችህ እና የገባህን ለማካፈል ላደረከው ቀናነት በእግዚያብሄር ስም አመሰግንሃለሁ።
ዮናዔል

3 መልሶች

+1 ድምጽ
ወንድሜ በመጀምርያ የጠየከው ነገር በጣም መስረታዊና ማንኛውም ክርስትያን ሊጠይቅው የሚገባ ጥያቄ ነው። የሚግርምህ ነገር ደሞ የህን ጥያቄ እየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር በተመላለሰበት ወቅት ብዙዎች በተለያየ መልኩ ጠይቀውት ነበር። ስለዚህ እራሱ የሰጠውን መልስ እንመልክት
ዮሓ 14፡8
ፊልጶስ። ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው።
ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ?
እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።
እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ።
///// ከኢየሱስ መልስ በግልጽ እንደምንረዳው እየሱስ እና አብ አንድ እንደሆኑ ነው። ባይሆን ኖሮ " አባቴ በሰማይ ነው እኔ እዚህ ነኝ" ማለት ይቀለው ነበር።
መጽሃፍ ቅዱስ በየትም ቦታ ቢሆን ስለ ሁለት ወይም ሶስት አካላት እንዳሉ አያስተመርም። ነገር ግን "በየይሁዳ መልእክት 1፡ 4 ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።" በማለት እየሱስ ክርስቶስ በስጋ የተገለጠውን አንዱን አምላክ የካዱትን ይቃወማል።
ማርቆስ ወንጌል 12፡29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥
ስለዚህ ወንድሜ ሁለት አምላክ አለ ካልን ፊተኛይቱን ትእዛዝ ጣስን ማለት ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ ማን ነው? ልትል ትችላለህ። እርግጥ ነው የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት በዚህ ምድር ሲመላልስ በነበረበት ወቅት ለነበሩም ሰዎች አነጋጋሪ ነበር። መጽሃፍ ቅዱስን ግን በቅንነት ስንመረምር እውነቱ ግልጽ ነው። ለማጠቃልል ያክል መጽሃፍ ቅዱስ በሰማይ አንድ ዙፋንና አንድ ተቀማጭ እንዳለ ያስረዳል "የዮሐንስ ራእይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤"
በተጨማሪ ..የዮሐንስ ራእይ 1፡8
ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ። አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።............18፡ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።
ወንደሜ ሆይ የጻፍኩትን ነገር ሁሉ በክርክር ሳይሆን በመማር መንፈስ እንድታየው እፈልጋለሁ። ተጨማሪ ጥያቄ ካለህ ጻፍልኝ። እግዚአብሔር ይባርክሀ!
4 ወራቶች በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
በመሰረቱ የአንተ አባባል ወጥ እና እርስ በራሱ ይማይጋጭ በመሁኑ ግልጽ ነው። ስለዚህም ልጠይቅሀ የምችለው ምንም የለም። ለመልስህም በጣም እግዚያብሄር ይስጥህ። ማየት እንደቻልክው እና ወንድማችን ፋንታጎንስ ሊያሳይ እንደሞከረው ያስርዳው ነገር ጥያቄወችን እዳነሳ አስገድዶኝ መልሶች ሳይገኙ በቀጣይ ለቀረቡትም መልስ ሳይሰጥ ወንድማችን ፋንታጎንስ የውሃ ሽታ ሆነዋል።

እሱ ባጭሩ የሚለው አዎ
1ኛ. አንድ አምላክ አለ(አብ) እኔም እስማማልሁ
2ኛ. እየሱስ ክርስቶስም አምላክ ነው እኔም ተስማማሁ
3ኛ.እግዚያብሄር አብ የአማልክቶች ሁሉ አምላክ ነው እየሱስ ክርስቶስንም ጨምሮ
ሁሉም የሚያመልኩት።

የኔ ጥያቄ ደግሞ
እግዝያብሄር አብ እና እየሱስ ክርስቶስ ሁልቱም አምላክ መሆናችዉ ካግባባን አንድ ሳይሆን ሁለት አማልክት መሆናችዉ አደለምን?

በአስርቱ ትእዛዛት እንደታዘዘው አንተም በ መ/ቅ እንዳሳየህው አንድ አምላክ ብቻ ለሚለው ትእዛዝ እንዴት እንግዛልን?

በተጨማሪም እየሱስ ክርስቶስን "አማላጅ" ነው ክሚለው አመለካከት ጋር እንድምን ማጣጣም ይቻላል (አምልክም፤ አማላጅም፤ የአምላክ ልጅም)?

ውድ ውንድሜ ቀደም ብየ እንደጠቀስኩት ለክርክር የሚበቃ እውቀት የለኝም። የራሴን መልኮታዊ እውቀት ልማስፋት እንጂ። ( ወንደሜ ሆይ የጻፍኩትን ነገር ሁሉ በክርክር ሳይሆን በመማር መንፈስ እንድታየው እፈልጋለሁ።)ላልክው ማልቴ ነው። በተረፈ ውንድማችንን ፋንታጎንስን ክጠፉበት ይመልስልን።
አሜን በያለሁ። I was so confused try to read what he wrote, I stop reading at all. I had to give him down vote.
ወይ ጉድ ያገራችን ሰዎች የሚሉት አባ ባል ነበር ምን ነበር፡ በሬው ወደዚያ ሽመሉ ....... ብቻ አንዱ ወዲህ ሌላው ወደዚያ ሆነበኝ።
) ተባረኩ
ወንድማችን ፋንታጎንስ

መገኘትህ አስደስቶኛል

አክባሪህ ዮናዔል
ሮሜ 8፡34 የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
ከሞትም በኋላ ለዘለአለም ለተቀበሉት ሁሉ ክርስቶስ ሊቀ ካህን ነው
ስልዚህ ክርስቶስ እየሱስ አማላጅ እና አማላጅ ብቻ ነው ማለት ነው? ወይስ እሱም አምላክ እግዚአብሄር አብም አምላክ አንድ ላይ ሁለት አማልክት? እንደገባኝ እርሶ የሚሉት ሊቀ ካህን ነው። ነው?

የቱን ነው እሱ?

ሊቀካህን፤ አማላጅ፤ ከአማልክት አንዱ ወይስ አምላክ?

እግዚያብሄር ይስጥልኝ
–2 ድምጾች
you know what i been following closely on what you are saying. the truth is
Jesus is all. He is God, all thing are created by him john1:3. He is the HIGH Priest and the lam that was sacrificed for our sin read the book of Hebrew.
The problem is we as human have to corner HIM one side only BUT HE< JESUS can't be cornered as HE is all. ሁሉ በ ሁሉ ነው። Let me ask you why can't he be both or all is it because your simple mind ( human mind) can't comprehend it or you are not willing to accept HIM as HE is. IF I was you I would repent my unbelief ask HIM to help me to believe.
3 ወራቶች በፊት ስም አልባ (7,060 ነጥቦች) የተመለሰ
3 ወራቶች በፊት የታረመ ስም አልባ
ወንድሜ/እሕቴ

ምን አልባት በአማርኛ ሳይሆን በፈረንጅኛ ሊገባው ይችላል ብለው አስበው ስለመለሱ አመሰግናልሁ። ሌላው ከመልሶት እንደገባኝ በጌታችን እና በመደሃኒታችን በ እየሱስ ክርስቶስ አምላክንትም ሊቀ ካህንንትም ያምናሉ። ግሩም ፤ በክርስቶስ የሚያምን ሰው ሌላውን ሰው ስላልገባው ነገር ወይንም ስላልተረዳው ነገር ሲያስተምረው " your simple mind can't comprehend it " እያለ ወይንም ብሎ በመናገሩ እሱ የክርስቶስ አማኝ ና ተክታይ መሆኑን ያሳያል እንዴ? ጌታችን ላንገላቱትና በጥፊ ለደበደቡት በፍቅር "የሚያረጉትን አያቁምና ይቅር በላችው" ነበር ያለው። በዚህ አጋጣሚ እኔ ከርሶ የተሻለ ክርስቲያናዊ ባህሪ አለኝ ለማለት እየሞክርኩ አይደለም። ትህትና የክርስትና መገልጫ መሆኑን አንርሳ ብዬ ወንድማዊ ሃሳቤን አጋርቼዎት አልፋልሁ።

I simply asked questions. Your answer didn't help me to grasp new knowldage. You said " you are not welling (you meant willing) to accept HIM as HE is.IF I was(you meant were) you I will repent my unbelief ask HIM to help me(You meant you) to believe."

So in your eys i am unbeliver, then say the word and make me belive.

God bless you.
–1 ድምጽ
ሰላም

እንዳዋቂስ አልመልስ ይህ ጥያቄ መጀመሪያ በ አርዮስ ተጠይቆ በ አንደኛው የ ኒስያ ስብሰባ በ 2000 በሚሆኒ ክርስቲያን አባቶች መልስ ተሰቶል። በርግጥ ጠያቂው ይህን ጠንቅቆ ማንበብ ይገባዋል።

ስለ ምንስ የ አርዮስ ሃሳብ በድጋሚ ይቀስቀሳል? ወይስ ጠያቂው የ አርያኒዝም ተከታይ ነውን? ክርስቶስን ፍጡር ሊለው ይወዳልን? ይህስ ባይሆን ለምንስ በድፍረት ስለፈጣሪ ምንነት ያወጋል? ከማንስ ጋር ሊያተካክለው ይወዳል?

ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡25፤ እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ።

እረ ተው እባካችሁን ፈጣሪን እንፍራ ስለሱስ በድፍረት አንመላልስ !!!

ትንቢተ ኢሳይያስ 55፡8-9
አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር።
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።


ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥

ሄኖክ
3 ወራቶች በፊት Henok (830 ነጥቦች) የተመለሰ
ፈጣሪን መፍራት በምግባር እንጂ ስለእርሱ ልናውቅ የሚገባንን ላለማወቅ በመጨፈን አይደለም!!! ስለአርዮስ ባነሳኸው ላይ የምለው ነገር ቢኖር በኒቅያ ጉባዔ የተሰበሰቡት 'አባቶች' መልስ መስጠትና ስለጉዳዩ መወያየት እግዚአብሔርን አለመፍራት ሊባል አይገባውም ወይ??????

እንደኔ አተያይ እግዚአብሔርን ሳይሆን የሃይማኖት ትምህርትን ወይም የኒቂያ ጉባዔ ሰዎችን ማክበርና መፍራትዎ እንጂ እውነተኛና ቀጥተኛ ልባዊ ጥያቄን መመለስዎ አይመስለኝም።
ስላም ፋንታጎንስ

እንደዛስ አይሁን። እኔስ ፈጣሪን እፈራለሁ እንጂ የስውን ስብስብ አልፈራም።

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ። ይሕንንስ ሳናውቅ አንመላለስ ብንመላለስም ወደ ስህተት እንወድቃለን!!!

ነገር ግን በዘመናችንም ይሁን ባለፉት ዘመናት ስለ ክርስቶስ ባህሪ የ ድፍረት ምርምር ብዙ ስህተት ፈጥሮል። አሁንም ጠያቂው በስው ልጅ ጠባብ አስተሳስብ 1+1=2 እያለ ሲል አምላክን እንድንፈራ ማሳስብስ ትክክል ኣይደለምን?

እኔስ ታሪክ አንብብ ያልኩት እንደዚ አይነት የድፍረት ቃል የት እንዳድረስን እንዲያውቅ ነብር። ነገር ግን አንተ እንደሚመስለኝ የ ቀድሞ ታሪክ ሲነሳ ትረበሻለ ይህ ከሆንስ መጽሃፍ ቅዱሱ እንዴት እንደተጠረዘ አንብብ።

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ /ምሳ. 1፥7/
እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል፤ /ምሳ. 8፥13/
እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ /ምሳ. 14፥27/
እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ትምህርት ነው፤ /ምሳ. 15፥33/
እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል /ምሳ. 19፥23/
እግዚአብሔርን የሚፈራ ከሁሉ ይወጣልና… ፡፡ /መክ. 7፥18/
እግዚአብሔርን ፍራ ትዕዛዙንም ጠብቅ፡፡ /መክ. 12፥13/
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ፍጻሜው ያምራል /ሲራ. 1፥13/
የጥበብ ዘውዷ እግዚአብሔርን መፍራት ነው /ሲራ. 1፥18/
እግዚአብሔርን መፍራት አትዘንጋ፡፡ /ሲራ. 1፥27/
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ለሕጉ ይገዛል /ሲራ. 35፥14/
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው መከራ አያገኘውም /ሲራ. 36፥1/
እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን /2ኛ ዜና. 19፥7/
እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፥ /መዝ. 24፥14/
እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ትንንሾችንና ትልልቆችን ይባርካል፡፡ /መዝ. 113፥21/

ሄኖክ
ወዳጄ ሄኖክ

በ እርሶ አይን "ደፋር እና እግዚያብሄርን የማይፈራ" መሆኔ አይገርምኝም። ፈራጅ እርሶ አደሉምና። በግሌ አባባሎትም ፍጽም ለ እግዚያብሄር ካሎት አክብሮት የተነሳ መሆኑን አልጠራጠርም። ይልቁንስ እግዚያብሄርን መፍራትና ማክብር እንዲሁም ማመን በተሰጠን አእምሮ መጠን እያወቅን መሆን አለበት። ጥያቄውቼም ለማውቅ ከመፈልግ እንጂ እንደርሶ ድምዳሜ እና ፍርድ ሳይሆን ሁሉንም እግዚያብሄር ያቀዋል።

የ አርዮስን ታሪክ ባይገርሞት (የ እርሶን ያክልም ባይሆን)ጠንቅቄ አውቀዋልሁ። በመሰረቱ ለጥያቄወቼ ምክነያቱም እየሱስ ክርስቶስን "ፍጡር" እና "ወልድ እንደማንኛዉም ተፍጥሩዋል። ስልዚህ ክሌላው የሚለይበት ምክነያት አይኖርም። ወልድ የሚኖረው እንደሁላችንም ሁሉ ቤግዚያብሄር ፍቃድ ነው" ክሚለዉና የለም ክርስቶስ እየሱስ አማላጅ እና አምላክ ነው (ሁለቱንም) ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከ ሰላሴ ትምህርት ጋር ይጋጫል። በዚህ ምክነያት ጥያቄወችን መላሼ ፋንታጎንስ ጥያቄዬ እንዲገባችው (እኔ እንደተረዳሁት አድርጌ 1+1...የሚለውን በማለቴ...) እግዚያብሄርን አለመፍራት ሳይሆን እሱን መፈለግ ነው። ሳላቀው ድግሞ ፍልጋ አስችጋሪ ነው። ለማውቅ ደግሞ ማንበብ መጠይቅ የግድ ነው ። ካሳዘንክዎት ይቅርታ።

ወንድሞት ዮናዔል
ዮናዔል ስላም ላንተ ይሁን

ወዳጄ ብለህኛል እና በድፍረት "አንተ" ልበልህ።

አዎን ፈራጅስ አንድ አምላክ ነው ፤ ነገር ግን እንደስው ፍጡር ስህተት ን ስናይ ስህተ እንላልን ፤ በርግጥ ስህተት ባዩም ተሳሳች ሊሆን ይችላል። እናም እኔስ ያልኩትን ብል ምንም አይግረምሕ ።

እኔ እግዚአብሔርን እንፍራ እያልኩ እምወተውታቹ እንዳንማርስ ሳልወድ አይደለም፤የተገለጠውንስ መማር ያስፈልጋል ፤ ማስተዋል ያለብን ግን እኛ ስለፈጣሪ የምናውቀው እሱ የገለጸልንን ብቻ ነው ሁሉንም ነገር ስለፈጣሪ አናውቅም ፡ ሙሴ እንዳለው
ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው። ኦሪት ዘዳግም29፤29 ስለዚሕ የተገለጸውንስ ለልጅ ልጆቻችን እናስተምር ።

ሌላው ማስተዋል ያለብን ስለ አብ ፡ ወልድ ፡ መንፍስ ቅዱስ ስናወራ ስለአንድ አምላክ የረቀቀ ክፍል እያወራን መሆኑን ነው ፤ ይሄንን ስናስብ እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ መሆኑን አውቀን ይሕን እንደመነሻ መጠቀም ይኖርብናል ። ቃል አጠቃቀማችንንም በጥንቃቄ መሆን ይገባዋል ። በ የማቴዎስ ወንጌል 12፡31 ክርስቶስ ያለውን እናስብ " ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም። "

በተጨማሪም ከ መጽሃፈ ኢሳያስ ከላይ ልጠቅስው እንደሞከርኩት አምላክ በስው ልጅ ጠባብ አስተሳስብ እና በሁሉም የተፈጠሩ ነገራት ሊገለጽ እንደማይችል መረዳት እንችላልን ፤ ተረድተንም እዚ ምድር ላይ ይሁን ፡ ስማያት ላይ ፡ወይንም አሳባችን ላይ በሚመጣ እውቀት (እንደ ቁጥር / ሂሳብ) አምላክን ሊገልጸው እንደማይችል እንረዳለን።

ይሄን ምክንያት በማድረግ መለኮታዊ ትምህርት በ ምሳሌወች ይገለጻሉ ምሳሌወቹም አምላክ ልንሸከመው እንችለዋልን ያለውን ይገልጹልናል። የዮሐንስ ወንጌል 16፡12 ክርስቶስ ያለውን እናስብ "የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም።


እስኪ ከዚ ምሳሌወች ምን ይገልጸልሃል?

የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1 1-5

1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
2 ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።
4 በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።
5 ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።



የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

ሄኖክ

ወንድሜ ሄኖክ

ምናልባት አገላለጼን እግዚያብሄርን ክመድፈር አድርገህ ተመልክተሕ ክሆነ የማወቅ/የእውቀት እጥረት እንዳለብኝ እያመንኩ ነገር ግን አለማወቄ ይህንን አይነት ድፍረት እንዳላሳደረብኝ እመነኝ። በተለይም አንተ የጠቀስከው አምላክን መዝለፍ ይቅርታ የሌለው ስህተት መሆኑ ለኔ ግልጽ ነው አንተም አስታውሰህኛል። ሊገቡን በሚችሉ ምሳሌዎች መጠቀሜ ለመግባቢያ ብቻ ነው። "መዝሙረ ዳዊት 86፡ 10 አቤቱ፥ ድንቅ የምታደርግ አንተ ታላቅ ነህና፥ አንተም ብቻህን ታላቅ አምላክ ነህና። 11 አቤቱ፥ መንገድህን ምራኝ፥ በእውነትህም እሄዳለሁ ስምህን ለመፍራት ልቤ ደስ ይለዋል። 12 አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ለዘላለምም ስምህን አከብራለሁ 13 ምሕረትህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍሴንም ከታችኛይቱ ሲኦል አድነሃታልና። " ወንድሜ ሄኖክ ይህ የልቤን ከሚገልጹልኝ አንዱ ሆኖ እንጂ ብዙ ጥቅሶች እንደሚኖሩ ይገባኛል ... መዝልፍ ግን.....ያን ያክል አላዋቂ አደለሁም። ስለ ማስታውስህ ግን እግዚያብሄር ይስጥልኝ።

ሌላው አንተ አጠር አርገህ ያሳየህው የስላሴ ትምህርት ወንድማችን ፋንታጎንስ እንደ አገላለጹ ቀደም ሲል ያምንበት የነበረው ነገር ግን አሁን በቀጣይነት የእኔን ጥያቄወች እየመለሰ አንተ ያልከውን "ሌላው ማስተዋል ያለብን ስለ አብ ፡ ወልድ ፡ መንፍስ ቅዱስ ስናወራ ስለአንድ አምላክ የረቀቀ ክፍል እያወራን መሆኑን ነው " የሚለውን ከላይ በተክታታይ ዕንዳየህው በተለይም "አንድ አምላክ" ሳይሆን የ አማልክት አምላክ እግዚያብሄር አብ እና ክሱ ቀጥሎ(የተመላኪነት መበላልጥ ኖርዋቸው) ጌታችንና መደሃኒታችን እንዲሁም አምላካችንን እየሱስ ክርስቶስን አምላክ ነው ነው የሚልው። ክላይ ያለውን ተክታትለሃል ብዬ ኣምናለሁ።

ማየት እንደቻልከውም ጥያቄወቼን እየመለስ ነው።

አምላካችንን ይብልጥ የምናቅብት መማማር የሁልን።

ወንድማችሁ ዮናዔል
ወንድም ዮናዔል

ሃሳቤን ስለተረዳህልኝ አመስግናለሁ።

አዎ የ ፋንታጎንስ መልሶች አንብቢያለሁ ፤ በ ይቀጥላል ስለቆመ ቀጣዩን እና ድምዳሜውን እንዴት እንደሚሆን ለማየት እየጠበኩ ነው።

እስካሁን ባነበብኩት በርግጥስ "ፋንታጎንስ" ወንድም ዮናዔልን እና ከ ዮናዔል የሚወጣውን ቃሉን አበላልጦ የሚጨርስ ይመስለኛል።

ከመገመት የሚቀጥለውን ክፍል ወይም መደምደሚያውን እየጠበኩ ነው።

ጸጋውን ያብዛልህ።

ሄኖክ።

የተዛመዱ ጥያቄዎች

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2012 by iyesus.com
Terms of use | Contact us