ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄና መልስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Friday, 18 May 2012
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

  • ይመዝገቡ

እግዚአብሄር በሰው ላይ መከራ ያመጣል ( በመከራ ሰውን ይፈትናል )???

4 ወራቶች በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

4 መልሶች

0 ድምጾች
ስላም ይሁንልወት.....እግዚአብሄር ስውን በመከራ አይፈትንም። ቅዱስ ቃሉ እንደሚለው የያዕቆብ መልእክት 1 ፡ 13 ማንም ሲፈተን በእግዚአብሄር እፈተናለሁ አይበል እግዚአብሄር በክፉ አይፈትንምና እርሱ እራሱስ ማንንም አይፈትንም። በእኔ መረዳት እዮብም በስይጣን ነው የተፈተነ። ከያዕቆብ መልእክት 4 ፡ 11 ላይ ቃሉ እንደሚነግረን ጌታ እራራለት እንጅ ፈተነው አይለንም ። በማቲወስ ወንጌል 6፡ 13 ላይ እግዚአብሔር ወልድ እንዴት እንደምንጸልይ ሲያስተምረን " ከክፉ አድነን እንጅ ወደ ፈተና አታግባን " ይህ ሃሳብ በአንድ መወስድ አለበት ነው ብየ አምናለሁ ክፉው ነው ወደ ፈተና የሚያስገባ ። ክፉ ሃሳባችን ምኞት የሰወች ክፉ ሃሳብ ክፉ መናፍስት ።
4 ወራቶች በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
እግዚአብሄር ሰዉን በክፉ አይፈትንም ነገር ግን የሰዉ ልጅ ክፉ ስራዉ ወደ መጥፎ ፈተና ወስዶ ዋጋ ሊያስከፍለዉ የችላል።ሰዉን በክፉ የሚፈትነዉ ግን ሰይጣን ነዉ።ኢዮብ በክፉ ስራዉ ሳይሆን ለኢግዚአብሄር ታማኝ ልብ ያለዉ ሰዉ ስለነበር በሰይጣን ተፈትኖአል።
ጌታ ግን ከዚህ መከራ ሁሉ ታድጎታል አስመልጦታል።
–1 ድምጽ
አዎን ይፈትናል...

እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ እስራኤልን በመከራ እንድትገባ አድርጓል። እኛም ብንሆን "ወደ ፈተና አታግባን" ብለን የምንጸልየው እግዚአብሔር ወደ ፈተና ሊያገባን እንደሚችል ስለምናውቅ አይደለምን?? በርግጥ መከራ ውስጥ ሲያስገባን የተለያዩ መሳሪያዎችን ይጠቀማል። ለምሳሌ-- ሰይጣንን (1ኛ ቆሮ 5፤5)
Quote:
መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።
ሰዎችን (በብዛት እስራኤልን በሶርያ ይቀጣ ነበር!!)
ድህነትን፤
Quote:
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
2፥6
እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል።
በሽታንና ሌሎችንም ይጠቀማል።

እዮብ ላይ መከራ ያመጣው እግዚአብሔር ሲሆን የተጠቀመበት ደግሞ ሰይጣንን ነው። ይህ መከራ የተዘጋጀው የእዮብን ታማኝነት ለመፈተን እንጂ ሰይጣንን ለማስደሰት አይደለም። ሰይጣንም ቢሆን ያለ እግዚአብሔር ፍቃድ አንዳች ስለማይችል ነው ወደ አምላክ በመቅረብ በእዮብ ላይ መከራ ለማምጣት ጥያቄ ያቀረበው።

ከምስጋና ጋር!!
ፋንታጎንስ
4 ወራቶች በፊት ቤሪያ (1,140 ነጥቦች) የተመለሰ
4 ወራቶች በፊት የታረመ ቤሪያ
0 ድምጾች
ተስፋ ለሁላችሁም

ምነው ሽክላ መሆናችንን ረስተህ ይህን በድፍረት ጠይቀሃል።

እሱስ እንድታቀው በ ትንቢተ ኢሳይያስ ይህን ይላል

5፤6፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም፤ በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።

7፤ ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ ደኅንነትን እሠራለሁክፋትንም እፈጥራለሁ፤ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።


ይህን በስተት እንዳትጠይቅ ደሞ በተቀጣይ ይህን ይላል

9፤ ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን። ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ። እጅ የለውም ይላልን?


እና ያ አንተ ልብ ላይ መከራ ያልከውን የፈጠረ አምላክን ምን ያመጣል ብለህስ አትጠይቅ!!!!!
3 ወራቶች በፊት Henok (830 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
አዎ እግዚአብሔር አማኞችን በመከራ በማሳለፍ እምነታቸውን test ያደርጋል።
1)ክዚህ ጊዜ በሁአላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው( ዘፍ 22፡1-12)
2)እግዚአብሔርም ሰይጣንን እነሆ ለእርሱ ያለው ሁሉ በእጅህ ነው ነገር ግን በርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ አለው (ኢዮብ 1፡12)
ሰይጣም መልሶ እግዚአብሔርን ቁርበት ስለ ቁርበት ነው ሰው ያለውን ሁሉ ስለ ሕይወቱ ይሰጣል ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሥጋውን ዳብስ በውነት በፊትህ ይሰድብሃል አለው።እግዚአብሔርም ሰይጣንን ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ እርሱ በጅህ ነው አለው (ኢዮብ 2፡4-7)
3)በዚያን ጊዜ ለመክራ አሳልፈው ይሰጡአችሁአል...እስከመጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል (ማቴ 24፡9-14)
4)ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችሁአልና ስለርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም።(ፊልጵ 1፡29)
5)...ይህም ብቻአይደለም ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ እንመካለን...(ሮሜ 5፡3-5)
6)..ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ ለምስጋና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችሁአል።(1ጴጥ 1፡6-7)
7)...እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወህኒ ሊያስገባችሁ አለው አስር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ፡ እስከ ሞት ድረስ የታመክ ሁን የሕይወትንም አክሊል እ ሰጥሃለሁ።(ራዕይ 2፡10-11)
3 ወራቶች በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
3 ወራቶች በፊት የታረመ ስም-አልባ

የተዛመዱ ጥያቄዎች

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2012 by iyesus.com
Terms of use | Contact us