ጽሑፏ እግዚአብሔርን በፍጹምና በቅን ልባቸው ለማወቅና ለመከተል ለሚፈልጉ፣ የእግዚአብሔርንም እውነት ለተራቡና ለተጠሙ የተዘጋጀች ናት::
"የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለ ምን ብዙ ይጦማሉ ጸሎትስ ስለ ምን ያደርጋሉ፥ ደግሞም የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ስለ ምን እንደዚሁ ያደርጋሉ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም?" ሉቃ 5፣33 ይህ የሃይማኖት ሰዎች ጥያቄና ኢየሱስም ለዚህ ጥያቄ የሰጠው መልስ፣ በኢየሱስ እና በሃይማኖት ሰዎች፣ እንዲሁም በአዲስ ኪዳን ሕይወትና በሃይማኖተኝነት መካከል ያለው የተራራቀ ልዩነት የታየበት ነው:: በኢየሱስ እና በሃይማኖት ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? ሃይማኖተኛ መሆንና ኢየሱስን መከተል ተመሳሳይ ነገር ነውን? ኢየሱስስ ደቀመዛሙርቱ ሃይማኖተኞች እንዲሆኑ ይፈልጋልን? እነዚህንና የመሳሰሉትን ወሳኝ መንፈሳዊ እውነቶችን የሚከተለውን መልእክት በመስማት ይመርምሩ::
መልእክቱን ያድምጡ |  Listen now